image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ ከተማ ጤና ጽ/ቤቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡት ጤና ጣቢያዎች የሽልማት እውቅና ሰጠ።

የካቲት 14/2018, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት የ6 ወር አፈጻጸሙን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ከገመገመ ቡኋላ በአፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት አምጥተዋል ያላቸውን ጤና ጣቢያዎችን በሽልማት ዛሬ እውቅና ሰቷል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መስፍን በየነ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት 6 ወራት ባብዛኛው የተሻለ የጤና አገልግሎት የሰጠንበት ቢሆንም የተወሰነ ክፍተትም ታይቷል ብለዋል። ሃላፊው ሲቀጥሉም በቀጣይ ጊዜያት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ ከስር እስር እየተከታተሉ በመቅረፍ ህብረተሰቡን በከፍታ ማገልገል አለብን ብለዋል። ለተሳታፊዎች ከመደረኩ የ2017 የ6 ወር ከ2018 በጀት አመት 6 ወር ጋር የነበረን አፈጻጸም በንጽጽር በማቅረብ የነበሩ ውጤቶችንና የታዩ ክፍተቶችን ለማሳየት ተሞክሯል። ተያይዞም የ6 ወር ቁልፍ ተግባራት ተለይተው ዝቅ ባሉት ላይ ዝቅ ያሉበት፣ የሚስተካከሉበት፣ ማን እና እንዴትመቼ መፈታት እንዳለባቸው አቅጣጫ ተሰቶባቸዋል። ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካቲት 13/2018 ዓ.ም

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች