image
image
image
image
image

የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በልደታ ክፍለ ከተማ ስር በአስሩም ወረዳዎች በይፋ መሰጠት ተጀመረ ።

ግንቦት 19, 2017
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ግንቦት 18/2017 ዓም የክትባት ዘመቻው የማስጀመሪያ ፕሮግራም በወረዳ 3 በአብነት ጤና ጣቢያ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተወካይ፣ የጤና የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/በት ኃላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ፣ የክፍለ ከተማው አመራር፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ወላጆች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ። የልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን የኩፍኝ በሽታ ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ክትባቱን መስጠት ነገ ሊደርስ የሚችለውን የጤና፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል። ሃላፊው አክለውም ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት በት/ቤቶች፣ በጊዚያዊ ጣቢያዎች እና በጤና ተቋማት ይሰጣል ያሉ ሲሆን ለዘመቻው መሳካት ሁሉም የሚመለከተው አካላት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል። የኩፍኝ በሽታ በኩፍኝ ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ እና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ሊተላላፍ የሚችል በሽታ ሲሆን አንድ በበሽታው የተያዘ ግለሰብ ከ12 እስከ 18 ለሚሆኑ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ በሽታው ማንኛውንም ሰው የሚያጠቃ ሲሆን በተለይም ዕድሜአቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ላይ በጣም የከፋ ከመሆኑም ባለፈ ሞትን ጨምሮ ለከፉ የጤና እክሎች ይዳርጋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ