image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ ሁለተኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ።

ታህሳስ 4, 2017
ሁለተኛ ዙር የህጻናት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በዛሬው እለት መጀመሩን የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት አስታውቋል። የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ እንደተናገሩት ከታህሳስ 3 እስከ 6/2017 ዓ.ም ለ4 ተከታታይ ቀናት በጤና ተቋማት፣ ቤት ለቤት እና በትምህርት ቤቶች እድሚያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ክትባቱ ይሰጣል ብለዋል፡፡ በአንደኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት የተሰጣቸው ህጻናት ሁለተኛው ዙር የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጣቸውም አቶ አህመድ ገልፀው ወላጆች ለክትባቱ ስኬታማነት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ