image
image
image
image
image

ባለፍት 6 ወራት ውጤታማ የጤና አገልግሎት መሰጠቱን የልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ገለጸ።

ጥር 12, 2017
ጽ/ቤቱ የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወር አፈፃፀሙን ገምግሟል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አህመድ እንድሪስ እንደተናገሩት ባለፍት 6 ወራት የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የጤና ተቋማት ውጤታማ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት እንዲችሉ ተሰርቷል ብለው ለዚህም ተገልጋዮች ስለተሰጣቸው አገልግሎቶች ምስክርነት እየሰጡ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የጤና ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን ፣የህክምና መሳሪያዎች ማሟላት፣ህብረተሰብን በማህበረሰብ አቅፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ እና ውጤት ተኮር ስራዎችን ማከናወን ባለፍት 6 ወራት በውጤታማነት የተሰሩ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል። የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ዘርፍ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስናቀች ደምሴ በበኩላቸው ጽ/ቤቱ እያከናወነው ስራ የሚበረታታ ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይ 6 ወራትም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው መሻሻሉን እና ህብረተሰቡ በተገቢው መልኩ እየተገለገለ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ