የልደታ ክፍለ ከተማ
ጤና ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
ጤና ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
ጤና ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
ጤና ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
ጤና ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
ጤና ጽ/ቤት

የልደታ ክፍለ ከተማ
ጤና ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

ጥራቱን የጠበቀ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ ጤና ማበልጸግ እና በሽታ መከላከል፤ የፈዉስ ህክምናና ተሃድሶ ጤና አገልግሎት ተልዕኮ እና ጤናማ፣ ምርታማና የበለጸገ ማኀበረሰብ የመፍጠር ራዕይን ዳር ለማድረስ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነምተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል እና አክሞ ማዳን፤ የእናቶች እና ህጻናት ሞት መቀነስ፤ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ዜጋ ማዳረስ ላይ መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተቀርጾ የህብረተሰቡን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ጥያቄ በተገቢ ሁኔታ ለመመለስ የተለያዩ ስትራቴጅክ እርምጃዎች ተቀርጸዉ እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡

የጤና ሴክተሩ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እና ተደራሽነትን በማሻሻል፤ በቴክኖሎጅ የተደገፈ ፈጣን እን ከብልሹ አሰራር የጸዳ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ሁለተኛዉ የጤናዉ ሴክተር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ .... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ አህመድ እንድረስ , የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

ዋና ዋና አገልግሎቶች

በሽታ መከላከልና መቆጣጠር አገልግሎት
ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር
🩺
የሜዲካል ህክምና አገልግሎት
የጥራት ማሻሻል አገልግሎት
የመሰረታዊ ጤና እና የጤና ኤክስቴንሽን
🚼
የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት
🔬
የመድሃኒትና ህክምና መሳርያዎች ግብአት አቅርቦት

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ የጤና ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡